
Ethiopia 2025/26 Harvest Update
The 2025/26 harvest is almost about to begin across Ethiopia, with cherries expected to reach full ripeness at varying times by altitude. Overall, the...
Market updates, education, partnership stories, and everything Ethiopian coffee

The 2025/26 harvest is almost about to begin across Ethiopia, with cherries expected to reach full ripeness at varying times by altitude. Overall, the...

Discover why Ethiopia stands out as the birthplace of coffee with unique geography and hundreds of heirloom varietals.
Latest insights from the world of Ethiopian coffee

The 2025/26 harvest is almost about to begin across Ethiopia, with cherries expected to reach full ripeness at varying times by altitude. Overall, the...

With approximately 11.6 million 60-kg bags forecast and exports nearing 288.2 billion Birr ($200.8 billion), Ethiopia must either transform its irrepl...

Addis Ababa, Ethiopia — November 25, 2025 — Marking a new era for Ethiopia’s coffee industry Specialty Coffee Association of Ethiopia (SCAE) is offici...

Discover why Ethiopia stands out as the birthplace of coffee with unique geography and hundreds of heirloom varietals.
Get the latest market insights, harvest reports, and coffee education delivered to your inbox
Stay updated with the latest announcements, market insights, and industry news from Ethiopia's official coffee and tea regulatory body.
የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ፤የ10 አመት የተከለሰ ኮምፕሬሄንሲቭ የቡና ስትራቴጂ ዕቅድም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።ነሐሴ 26/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣ ከቡና ሻይና ቅመማ ቅመም አብቃይ ክልሎች እና የባለስልጣኑ አመራሮች በታደሙበት መድረክ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ10 አመት የተከለሰ ኮምፕሬሄንሲቭ የቡና ስትራቴጂ ዕቅድ ላይ የግምገማና ውይይት መድረክ አካሂዷል።በመድረኩ መክፈቻ ላይ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ልማት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ ንግግር አሰምተዋል። በንግግራቸው ያለባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የታቀደ ከዳር እንደማይደር ስለሚታወቅና የተገኘውም የክንውን ውጤት በመድረኩ በታደሙ አካላት እና በቡና ተዋናዩ ጥረት ስለሆነ በጋራ ለመነጋገር መድረኩ እንደተዘጋጀ ተናግረዋል። ከተዘጋጀ ፓኬጅ የተቀዱ በአንገብጋቢነት የሚለዩ የቡና ኢኒሼቲቮች እንዳሉ የተናገሩት ኃላፊው ወደአርሷደሩ እንደወረደ ገልጸዋል፤ በጉዳዩ ላይም ስልጠና ይሰጣል ብለዋል።በማስከተልም አቶ ቦንሳ መርጋ የባለስልጣኑ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ዕቅድ አፈጻጸሙን አቅርበዋል። ሲያቀርቡም 1.6 ሚሊዮን ሄክታር በቡና እንደተሸፈነ ገልጸው ከአምናው አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል። የምርት አፈጻጸሙን ሲያቀርቡም 1.5 ሚሊዮን 80 ሺ ቶን እንደሆነ ተናግረው ምርታማነት 9.4 ኩንታል በሄክታር እንደሆነ ገልጸዋል።ከላይ የተጠቀሱት ውጤቶች የተመዘገቡበት ምክንያቶችን ሲናገሩ በአዲስ ቡና ተከላ፣ በማሳ እንክብካቤ፣ በጉንደላ እና በነቅሎ ተከላ ላይ ስራዎች በመሰራታቸው ነው ብለዋል። በቀጣይም ጉንደላና ነቅሎ ተከላ ላይ በይበልጥ መሠራት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።በተመሳሳይ መልኩ በሻይውና በቅመማቅመም ሰብሎች ላይ ያለውን አፈጻጸም አቅርበዋል።የኤክስፖርት አፈጻጸሙን ሲያቀርቡም 40 በመቶ የዓለም ዋጋ በቀነሰበት፣ የሆርሙዝ ክስተት በታየበት፣ የነዳጅ ዋጋ በናረበት፣ የብራዚል ቡና በገፍ ወደገበያ በገባበት ሁኔታ የታቀደው 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተሳክቷል ብለዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን ከታቀደው የቡና መጠን ያነሰ ተልኮ መሳካቱም ስኬቱን ለየት ያደርገዋል ብለዋል። በዚህ ሁሉ ተግዳሮቶች ውስጥ ለመጣውም ውጤት ምክንያቶቹን ሲያቀርቡም ከጀረጃ 1 እስከ ደረጃ 3 ያሉ ቡናዎች መጠን እና ዋጋቸው መጨመር መሆኑን ጠቅሰው ይህ ምን ያህል የቡና ጥራት ላይ ውጤታማ ስራ እንደተሰራ ማሳያ ነው ብለዋል።በማስከተልም ስትራቴጂ ዕቅዱ ቀርቦ በሁለቱም አጀንዳዎች ላይ ሐሳቦች ከታዳሚው ተሰንዝረው የመድረኩ ፍጻሜ ሆኗል።አሸናፊ ጌታሁን እንደዘገበው


በ #ፓኪስታን #ኢስላማባድ ለመጀመሪያ ጊዜ የ #ኢትዮጵያ ቡና መሸጫ ካፌ ተከፈተበእስላማባድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመንታ ከተሞች እስላማባድ እና ራዋልፒንዲ የመጀመሪያው የሆነው የኢትዮጵያ ቡና ካፌ መከፈቱን አስታወቀ።በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን (ዶ/ር) እሁድ ዕለት ባካሄዱት የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት፣ የኤምባሲው ሠራተኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ተወካዮች በተገኙበት በባህላዊ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት ካፌውን መርቀው ከፍተዋል።አምባሳደሩ በምረቃው ወቅት እንደገለፁት፣ ካፌው መከፈቱ በኢትዮጵያ እና በፓኪስታን መካከል እያደገ ከመጣው ሁለትዮሽ ግንኙነት ጎን ለጎን የባህል እና ሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከር አዲስ መንገድ ይከፍታል።https://www.facebook.com/share/p/1CHvfNAmPG/በ #ፓኪስታን #ኢስላማባድ ለመጀመሪያ ጊዜ የ #ኢትዮጵያ ቡና መሸጫ ካፌ ተከፈተበእስላማባድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመንታ ከተሞች እስላማባድ እና ራዋልፒንዲ የመጀመሪያው የሆነው የኢትዮጵያ ቡና ካፌ መከፈቱን አስታወቀ።በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን (ዶ/ር) እሁድ ዕለት ባካሄዱት የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት፣ የኤምባሲው ሠራተኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ተወካዮች በተገኙበት በባህላዊ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት ካፌውን መርቀው ከፍተዋል።አምባሳደሩ በምረቃው ወቅት እንደገለፁት፣ ካፌው መከፈቱ በኢትዮጵያ እና በፓኪስታን መካከል እያደገ ከመጣው ሁለትዮሽ ግንኙነት ጎን ለጎን የባህል እና ሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከር አዲስ መንገድ ይከፍታል።https://www.facebook.com/share/p/1CHvfNAmPG/
ሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በሙዳ–ድኖቆሰ ቀበሌ በአርሶ አደር ጓሮ እየለማ የሚገኘው የቡና ልማት በአሁኑ ወቅት አበረታች ገጽታ እያሳየ ይገኛል።በተለይም በቡና ዛፎቹ ላይ በብዛት የተያዙ የቡና ፍሬዎች የልማቱን የምርት አቅም የሚያሳይ ሲሆን፣ በጓሮ ልማት ውስጥ ከበቆሎና ሌሎች ሰብሎች ጋር ተቀናጅቶ መልማቱም የመሬት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ ነው። የጓሮ ቡና ልማት ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩም በላይ የቤተሰብ ኢኮኖሚን በማጠናከር የአካባቢውን የቡና ምርት አቅም ለማሳደግ የሚጫወተው ሚና የጎላ ነው።በዚህም መነሻነት የቡና ችግኝ ማፍላት፣ በተገቢው የአተካከል ዘዴ መትከል፣ የእርሻ እንክብካቤን ማጠናከር እና የተቀናጀ የቡና ልማትን ማስፋፋት ለቀጣይ የምርት ዕድገት ወሳኝ ናቸው።በሙዳ–ድኖቆሰ ቀበሌ የሚታየው ይህ የቡና ልማት ገጽታ በጓሮ ልማት የተሻለ ምርትና የተሻለ ገቢ ለማምጣት የሚቻል መሆኑን የሚያሳይ አበረታች ምሳሌ ነው። መረጃው የሙደ ድኖቆሳ ቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ነው።


የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል።መልካም በዓል!!!